የኢትዮጵያዊያኑ ሠልፍ በመንግሥታቱ ድርጅት ደጅ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ - ኒው ዮርክ




Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያዊያኑ ሠልፍ በመንግሥታቱ ድርጅት ደጅ


ከተለያዩ የሲቪክ ማኅበራትና የፖለቲካ ድርጅቶች የተውጣጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልድ ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ትናንት በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት በኢትዮጵያ ይካሄዳሉ ስላሏቸው የመብት ጥሰቶች የተቃውሞ ሠልፍ አካሂደዋል።

በተለይ የሕዝቦችን ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀል አስመልክቶ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ መሆኑን፣ ለዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማመልከት እንደሆነ ከሠልፉ አዘጋጅና አስተባባሪዎች አንዱ ለዝግጅት ክፍላቸን ገልፀዋል።

ሕዝቦችን ማፈናቀል ሕገወጥ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ባለፈው ሣምንት ለፓርላማ ባደረጉት ንግግር መግለፃቸው ይታወሳል።

በኒው ዮርክ በተካሄደው ሠልፍ ላይ የተካፈሉት ከዋሽንግተን ዲ.ሲ.ና አካባቢዋ በሁለት አውቶቡሶችና በአነስተኛ መኪኖች ወደ ከተማዋ የተጓዙና የኒው ዮርክ ከተማ ነዋሪዎች መሆናቸውን አዘጋጆቹ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

ለዝርዝር መረጃ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ