ሃዘንን እንዴት እንቋቋም? - ስነ-ልቦናዊ ጤና
Your browser doesn’t support HTML5
ይህ ያለንበት ወቅት በዓለም ዙሪያ ብዙ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ለውጦች የሚካሄዱበት እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ በርሃብ እና በጦርነት ምክንያት ብዙ ሕልፈቶች እያጋጠሙ ያለበት ነው፡፡ በኢትዮጵያም በተመሳሳይ የሰዎች ሕልፈት፣ መፈናቀል እና የተለያዩ ሃዘንን የሚያጭሩ ጉዳዮች እንደሃገር እያስተናገደች ትገኛለች፡፡ ሃገራት ወደፊት እንዲጓዙም ግለሰቦች በተገቢው መንገድ ሃዘናቸውን መወጣት እንዳለባቸው የስነ-ልቦና ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡