በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚኒስቴር ዲኤታ ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ሙኒር ካሳ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስተሩ የሆነ ከፍተኛ ቡድን መቁዋቁዋሙን እና ቫይረሱ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት በሙሉ መደረጉን ለአሜሪካን ድምጽ ገልጸዋል፡፡ በቻይና ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችም የምግብ እና አስፈላጊው ትብብር እና እርዳታ እንዲደረግላቸው ጤና ጥበቃ ሚኒስተር በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ጋር ውይይት ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡
ኖቬል ኮሮናቫይረስ ወደ አገር እንዳይገባ አስፈለጊውን ዝግጅት አድርገናል
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያ ውስጥ የኖቬል ኮሮና ቫይረስ እስካሁን ደረስ እንደልተገኘ እና ከውሃን ወደ አአ ተሳፍረው የተገኙ አራት ሰዎችም ከቻይና ለሚመጡ ተጉዋዦች በተለየ በማቆያ ስፍራ ተለይተው እየተጠበቁ መሆናቸውን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቆዋል፡፡