በሰሜን ወሎ የተጣሉ ፈንጂዎች እያደረሱ ያሉት ጉዳት

Your browser doesn’t support HTML5

የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረው በቆዩትና ጦርነት ሲካሄድባቸው በነበሩ የሰሜን ወሎ ዞን አካባቢዎች በርካታ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች በየአካባቢው ተቀብረውና ተጥለው እንደሚገኙ ያስታወቀው የዞኑ ፖሊስ ህዝቡ ራሱን ከአደጋ እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

በየቦታው ተጥለውና ተቀብረው የሚገኙ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች በሰው ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት እያደረሱ መሆኑን ፖሊስ አስታወቋል፡፡

ተቀጣጣይ የጦር መሳሪያዎቸን በማመከን የአደጋውን መጠን ለመቀነስ ዞኑ ለሚመለከተው አካል የድጋፍ ጥያቄ ማቅረቡን ነው ፖሊስ ያስረዳው፡፡

[ሙሉውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ]