ሰሜን ኮርያ እና ዩናይትድ ስቴትስ

Your browser doesn’t support HTML5

ሰሜን ኮርያ የዩናይትድ ስቴትስ የፓሲፊክ ግዛት በሆነው ጉዋም ላይ የሚሳይል ጥቃት ለመክፈት “በጥንቃቄ እየመረመርኩ ነው” ስትል ዛሬ በመናገርዋ በዩናይትድ ስቴትስና በሰሜን ኮርያ መካከል ወታደራዊ ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚለው ስጋት መባባሱ ቀጥሏል። ሰሜን ኮርያ ይህን ምላሽ የሰጠችው የአሜርካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ዓይነት ዛቻ “የእሳትና የቁጣ ምላሽ ያገኛል” የሚል ዛቻ ካሰሙ ሰዓታት በኋል ነው።