በጦርነት ተፈናቅለው የቆዩ ወገኖችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜኑ ጦርነት ሳቢያ ከአላማጣና አካባቢዋ ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ድሌሮቃ መጠለያ ጣቢያ የነበሩ ከ30 ሽህ በላይ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ መጀመሩን የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር አስታወቀ፡፡

ወደ አካባቢያቸው መመለሳቸው እንዳስደሰታቸው የገለፁት ተፈናቃዮቹ "ጥለነው የሄድነው ንብረት ስለተዘረፈና ስለወደመ ህይወትን እንደ አዲስ ለመመስረት መገደዳቸውን ይናገራሉ።