የናይል ተፋሰስ ሃገሮች ግብፅ እንድትመለስ ጠየቁ

የናይል ተፋሰስ




አቶ ተፈራ በየነ፤ የናይል ወንዝ ትብብር ጅማሮ /ኤንቢአይ/ ዋና ዳይሬክተር


Your browser doesn’t support HTML5

ከአቶ ተፈራ በየነ፤ የናይል ወንዝ ትብብር ጅማሮ /ኤንቢአይ/ ዋና ዳይሬክተር ጋር የደረገ ሙሉ ቃለ-ምልልስ


Your browser doesn’t support HTML5

የናይል ተፋሰስ ሃገሮች ግብፅ እንድትመለስ ጠየቁ



ጁባ - ደቡብ ሱዳን

ባለፈው ሣምንት ማብቂያ ላይ ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ውስጥ የተሰበሰቡት የናይል ወንዝ የትብብር ጅማሮ ወይም ናይል ቤዚን ኢኒሼቲቭ የውኃ ሚኒስትሮች ግብፅ ወደ ትብብር መድረኩ አባልነት እንድትመለስ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ ሱዳን አቋርጣው ወደነበረው የኢኒሼቲቩ አባልነቷ ሙሉ የመዋጮ ውዝፍ ዕዳዋን ከፍላ መመለሷን ዋና ፅሕፈት ቤቱ ካምፓላ-ዩጋንዳ የሚገኘው የናይል ትብብር አካባቢያዊ ድርጅቱ /ኤንቢአይ/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ በየነ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልፀዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ

በሌላ በኩል ደግሞ በሰባት የናይል ቤዚን ወይም የናይል ተፋሰስ ሃገሮች የተፈረመውንና እስከአሁን ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሃገሮች በየፓርላማዎቻቸው ያፀደቁትን የናይል ተፋሰስ ትብብር ማዕቀፍ ስምምነት ዩጋንዳም ልታፀድቀው መሆኑን የሃገሪቱ የውኃና የአካባቢ ሚኒስትር መናገራቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሃገሮች

የናይል ተፋሰስ ሃገሮች የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ፣ ዩጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ርዋንዳ፣ ቡሩንዲ፣ ኬንያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ግብፅ ሲሆኑ ኤርትራ በራሷ ፍላጎት ታዛቢ በመሆኗና ግብፅና ሱዳን የስምምነቱን አንቀፅ 14(b)ን በመቃወማቸው አለመፈረማቸው ይታወቃል፡፡

የናይል ተፋሰስ ሃገሮች

ግብፅ የስምምነቱ አንቀፅ 14(b) የውኃ ደኅንነቴን ይጎዳል ትላለች፡፡

ቀደም ሲል እአአ በ1929 ዓ.ም እንግሊዝ ደንግጋው የነበረ “ውል” የአባይን የውኃ ተጠቃሚነት በአብዛኛውና አንዳንዴም ሙሉ በሙሉ ለግብፅ ይሰጥ የነበረና በራስጌው የተፋሰሱ ሃገሮች ውስጥ የሚታሰቡ አባይ ወይም ናይል ወንዝን የሚመለከቱ ወይም ሊነኩ የሚችሉ ፕሮጀክቶችን ሁሉ የማስቆም ሥልጣን ያቀዳጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡

አባይ በካይሮ


ከአቶ ተፈራ በየነ ጋር የተደረገውን ሙሉ ቃለ ምልልስ እና የዜናውን ፋይሎች ያዳምጡ፡፡