በናይጄሪያ በገበሬዎች ላይ የተፈጽመ ጥቃት የምግብ እጥረት የፈጥራል የሚል ሥጋት አሳድሯል

Your browser doesn’t support HTML5

በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ በምትገኝ ካትሲና በተባለች ክፍለ ግዛት ታጣቂ ሽፍቶች 12 ስዎችን ገድለው የእርሻ ማሳ ማቃጠላቸውን ተከትሎ ፖሊስ ህግ አስከባሪ ኃይሎችን ወደ ስፍራው ስልክ የሃገሪቱ ወታደሮች ደግሞ በቦርኖ ግዛት እሁድ ዕለት 50 ገበሬዎች የተገደሉበትን ሁኔታ እየመረመሩ ይገኛል።

የካትሲና ክፍለ ግዛት የፖሊስ ቃል አቀባይ ጋምቦ ኢሳ እንዳሉት የማክሰኞውን ጥቃት ተከትሎ ሁኔታዎችን ለማረጋጋት የጸጥታ ኃይሎች ወደ ጉካርዲ መንደር ተልከዋል።

ቃል አቀባዩ እንዳሉት የፖሊስ ኮሚሽነሩ አካባቢውን ሲጎበኙ ፖሊስ ጉዳዩን በቅርብ እየተከታተለው ነው ሲሉ ነዋሪዎችን አረጋግተዋል።

ቲመቲ ኦቢይዙ ከአቡጃ ለቪኦኤ የላከውን ዘገባ እንግዱ ወልዴ ወደ አማርኛ መልሶታል።