የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ለአጋቾች የማስለቀቂያ ቤዛ እንዳይከፈል አዘዙ

Your browser doesn’t support HTML5

በናይጄሪያ፣ ባለፈው ሳምንት በታጣቂዎች ለተጠለፉት ከ250 ለሚበልጡ ተማሪዎች፣ የመንግሥቱ የጸጥታ ኀይሎች ፈጽሞ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንዳይከፍሉ፣ ፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ ትዕዛዝ እንደሰጡ የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር ተናገሩ፡፡

ሚኒስትሩ፣ ትላንት ረቡዕ በሰጡት ቃል፣ “ማስለቀቂያ አይከፈልም፤ የተጠለፉትም ልጆች በሙሉ እንዲለቀቁ ይደረጋል፤” ብለዋል። የተጠላፊዎቹ ቤተሰቦች በበኩላቸው፣ ጠላፊዎቹ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ ከሰሜን ናይጄሪያ ካዱና ክፍለ ግዛት ኩሪጋ መንደር ለጠለፏቸው ተማሪዎች ማስለቀቂያ ብዙ ገንዘብ እንደጠየቋቸው ገልጸዋል፡፡የቪኦኤውን ማይክል ብራውን ጥንቅር፣ ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እና ከሮይተርስ ዘገባዎች ጋራ የተቀናጀውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።