የአሜሪካው ኦስተንና የኔቶው ሽቶልተንበርግ ተገናኙ

Your browser doesn’t support HTML5

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ዛሬ ብራስልስ ላይ ከሰሜን አትላንቲክ የጦር ትብብር ድርጅት /ኔቶ/ ዋና ፀሃፊ የንስ ሽቶልተንበርግ ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ የኔቶን ምሥራቃዊ አቅም ለማጠናከር ተጨማሪ ወታደሮችን በመላኳና ስለቁርጠኛነቷም ዋና ፀሃፊው አድናቆታቸውን ገልፀው ለውጥረቱ የፖለቲካና ዲፕሎማሲያዊ መፍትኄ ለማፈላለግ ከሩሲያ ጋር መነጋገራቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

ሩሲያ ጦሯን ከዩክሬን አዋሳኝ አካባቢዎች እየሳበች መሆኗን ብታሳውቅም እውነት ስለመሆኑ ማረጋገጫ እንደሌላቸው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ማለዳ ላይ ተናግረዋል።