ከኢትዮጵያ ጋር በሚያዋስነው የኬኒያ ማርሳቢት ክፍለ ግዛት በጎሳ ግጭት ሳቢያ ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የኬኒያ ባለሥልጣናት በሽዎች የተቆጠሩ ፖሊሶች እና የፀጥታ ኃይሎች በአካባቢው አሰማርተዋል፡፡ የኬኒያ ባለሥልጣናት በተጨማሪም በቀንድ ከብት ዝርፊያ እና ከኢትዮጵያ በድብቅ በሚገቡ የጦር መሳሪያዎች በሚታወቀው አካባቢ ለአንድ ወር የሚቆይ የሌሊት ሰዓት እላፊ ማወጃቸውን ጠቅሳ ከናይሮቢ ቪክቶሪያ አሙንጋ የላከችውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች፡፡