የባይቶናውን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ እንዳልተረከበ ፌዴራል ፖሊስ ገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

የትግራዩን ተቃዋሚ የባይቶና ፓርቲን የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብሮም በርሄንና ከእርሳቸው ጋር የተያዙ ሃያ እሥረኞችን አለመረከቡን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ዛሬ ለፍርድ ቤት ገለፀ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ አቶ ክብሮምን ለፌዴራል ፖሊስ ያስረከበበትን ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ እንዲያቀርም ፌደራል ፖሊስ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

የተጠርጣሪ ቤተሰቦች በበኩላቸው እሥረኞቹ ያሉበት ያለመታወቅ እንዳሳሰባቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።