በግድያ የተጠረጠሩ የነቀምቴ ከንቲባ እና ሌሎችም ባለሥልጣናት ታሰሩ

Your browser doesn’t support HTML5

የነቀምቴ ከተማ ከንቲባ አቶ ቶሌራ ረጋሳ መታሰራቸውን ባለቤታቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

አንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የከተማ አስተዳደሩ ሠራተኛ፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ፣ በብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ሓላፊ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ፣ በርካታ የከተማው ባለሥልጣናት እና የመንግሥት ሠራተኞች መታሰራቸውን ገልጸዋል።

በዚኽ ዙሪያ፣ ከከተማውም ኾነ ከኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።