የቪኦኤ አድማጮች ምርጫ ቦርድን ይጠይቃሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ሚናና ኃላፊነት ላይ ጥያቄዎች ቀረቡ፡፡ ነጋ ዱፊሳ ይመልሳሉ፡፡በኢትዮጵያ የምርጫ ቦርድ ሚናና ኃላፊነት ላይ ጥያቄዎች ቀረቡ፡፡ ነጋ ዱፊሳ ይመልሳሉ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

የቪኦኤ አድማጮች ምርጫ ቦርድን ይጠይቃሉ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ እንዲሁም የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ፓርቲ ውስጥ አለ የተባለውን ክፍፍል ተከትሎ በአቶ ትዕግስቱ አወሉና በአቶ አበባው መሃሪ ለሚመሩት ወገኖች ዕውቅና መስጠቱን ተከትሎ የቦርዱን ዋና ፀሐፊና የፅህፈት ቤቱን ዋና ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፊሳን ለውይይት ጋብዘናል።

በርካታ አድማጮች ቦርዱ እርምጃውን ለመውሰድ ያለው ሕጋዊ ሥልጣን ምን እንደሆነ በመጠየቅ ውሳኔው የተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያዳክምና ለገዥው ፓርቲ የሚያደላ ነው ሲሉ ተችተዋል።

በሌላ በኩል ፓርቲዎቹ በመካከላቸው የተፈጠረውን መከፋፋል በሰላም መፍታት ካልቻሉ ቦርዱ ቀደም ብሎ ከምርጫው ሂደት ማስወገዱ ተገቢ ነው በማለት የደገፉም አሉ።

አቶ ከአድማጮች ለቀረቡ ጥያቄዎች መልስ ሰጥተዋል፤ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡