በፓኪስታን የታሊባን ጦር ሠፈር ለአፍጋኒስታን ሠላምና የመረጋጋት ስጋት

  • ቪኦኤ ዜና

የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ፀኃፊ ጄንስ ስቶልንበርግ

ፓኪስታን ውስጥ የሚገኘው የታሊባን ጦር ሠፈር፣ አፍጋኒስታን ውስጥ ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን ለተያዘው ጥረት ደንቃራ ነው ሲሉ፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ፀኃፊ ጄንስ ስቶልንበርግ አስታወቁ።

ፓኪስታን ውስጥ የሚገኘው የታሊባን ጦር ሠፈር፣ አፍጋኒስታን ውስጥ ሠላምና መረጋጋት ለማስፈን ለተያዘው ጥረት ደንቃራ ነው ሲሉ፣ የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃልኪዳን ድርጅት ኔቶ ዋና ፀኃፊ ጄንስ ስቶልንበርግ አስታወቁ።

ሚስተር ስቶልንበርግ ይህን ያስታወቁት፣ ዛሬ ማክሰኞ የኔቶ አባላት ጄኔቫ ውስጥ በሚገኘው ዋና ቢሮው በተሰበሰቡበት ወቅት ሲሆን፣ ዋና ፀኃፊው የፓኪስታን መሪዎች በሚገኙበት ይህን በመሰለው ስብሰባ ሁሉ ተመሳሳይ ማሳሰቢያ እንደሚሰጡ ይታወቃል።

የኔቶው ኃላፊ በዚሁ ማሳሰቢያቸው፣ አባል ሀገሮች በሙሉ የአፍጋኒስታንን ሠላም መደገፍና ይልቁንም ለዚህ ነውጠኛ ቡድን ከለላ ከመሥጠት እንዲታቀቡ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ስቶልንበርግ አስለያየታቸውን የሰጡት፣ የፓኪስታኗ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር፣ ሸብርተኞች ሀገራቸው ውስጥ እንደማይንቀሳቀሱ ኦፊሴላዊ ማስተባበያ ከሰጡ ከሰዓታት በኋላ ነው።