ፀረ-ሽብር ስብሰባ ናይሮቢ ላይ ይካሄዳል

  • ቪኦኤ ዜና

የቻድ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ እና የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ለፀረ-ሽብር ስብሰባው ናይሮቢ ይገኛሉ

መላ አፍሪካ ውስጥ ሽብር ፈጠራንና ፅንኝነትን መዋጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ለመምከር የአፍሪካ መሪዎች ነገ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ይሰበሰባሉ፡፡ ተቃዋሚዎችን በሽብር ፈጣሪነት መፈረጅና መወንጀል አደጋ አለው ሲሉ አንድ አፍሪካዊ ባለሙያ አስጠንቅቀዋል፡፡

መላ አፍሪካ ውስጥ ሽብር ፈጠራንና ፅንኝነትን መዋጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ለመምከር የአፍሪካ መሪዎች ነገ ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ላይ ይሰበሰባሉ፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ስብሰባ በአፍሪካ ኅብረት ሲዘጋጅ የአሁኑ መጀመሪያው መሆኑም ተገልጿል፡፡

በናይሮቢው ጉባዔ ላይ የሚገኙት የስድስት የአፍሪካ ሃገሮች - የናይጀሪያ፣ የቻድ፣ የኒዠር፣ የኬንያ፣ የታንዛኒያና የሶማሊያ መሪዎች ናቸው፡፡ ማንነታቸው በዝርዝር ባይገለፅም የሌሎች ሃገሮች መሪዎችም ይገኛሉ ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ሕብረት

ይህ ስብሰባ አፍሪካ ፀረ-አፓርታይድ ትግሏን እንድታሣልጥና እንድታጠናክር፣ እንዲሁም አጎራባች ሃገሮች የመረጃ ልውውጣቸውን እንዲያሰፉና እንዲያሻሽሉ ዕድል ይሰጣቸዋል ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ፀረ-ሽብር ባለሥልጣን አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴይራ ገልፀዋል፡፡

ተቃዋሚዎችን በሽብር ፈጣሪነት መፈረጅና መወንጀል አደጋ አለው ሲሉ አንድ አፍሪካዊ ባለሙያ አስጠንቅቀዋል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡