ሳን ሱኪ በወታደራዊ መንግሥቱ አራት ዓመት ተፈረደባቸው

  • ቪኦኤ ዜና

ፎቶ ፋይል፦ ኦን ሳን ሱኪ

የማያንማር ወታደራዊ መንግሥት ያሰራቸው የቀድሞ የማያንማር መሪ ኦን ሳን ሱኪ፣ ዛሬ ሰኞ የአራት ዓመት እስራ የተፈረደባቸው መሆኑን የመንግሥት ቃል አቀባይን ጠቅሶ አሶሼይትድ ፕሬስ ዘገበ፡፡

የ76 ዓመቷ ሳን ሱኪ የተፈረደባቸው በወታደራዊ መንግሥት ላይ አመጽ ቀስቅሰዋል፣ የኮቪድ-19ን ደንቦች ጥሰዋል በሚሉ ሁለት ክሶች ነው፡፡

በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጡት ሳን ሱኪ ባለፈው የካቲት አሁን ባለው ወታደራዊ ኃይል ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ በርካታ ክሶች ሲቀርብባቸው ቆይቷል፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ለበርካታ አስርት ዓመታት በሥልጣን ላይ የኖረውን የማያንማር ወታደራዊ ኃይል እርምጃ በማውገዝ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው፡፡