በሞጣ ከተማ መስጊዶች ቃጠሎ ተጠርጣሪዎች ቁጥር መጨመሩ ተጠቆመ

Your browser doesn’t support HTML5

ሞጣ ከተማ ውስጥ ከደረሰው የመስጊዶች ቃጠሎ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 27 መድረሱን የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ አስታውቋል። የተቃጠሉትን መስጊዶች መልሶ ለመገንባት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑንም የፖሊስ አዛዡ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።