በአዋጁ የተያዙ ሰዎች ጉዳይ ፈጥኖ እንደሚታይ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የተያዙ ወይም የታሰሩ ሰዎች ጉዳዮች በመደበኛው የፍትህ ሥርዓት በአፋጣኝ እልባት እንደሚያገኝ የፍትህ ሚኒስቴር የፕሬስ ኃላፊ አቶ አወል ሡልጣን ለቪኦኤ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪና የአንዳንዶቹ እስረኞች ጠበቃ የሆኑት አቶ ከበደ አሰፋ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል "የትግራይ ተወላጆች የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ከሚደነግገው ውጭ መታሠራቸውን፣ በጤናና በምግብ ችግር መጎሳቆላቸውን፣ ብዙዎቹ ቢለቀቁም እስከአሁንም ያልተፈቱ መኖራቸውን፣ ወደ ንግድ ሥራቸው መመለስ የሚፈልጉ ቢኖሩም የበታች ባለሥልጣኖች እንደማይተባበሯቸው” ተናግረዋል።

ከትግራይ ታጣቂዎች ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌላቸው የተናገሩ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ “በማንነታቸው ብቻ መታሰራቸውን” አመልክተዋል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት የታሰሩ ሰዎች ሁሉ እንዲለቀቁ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ እንዲሁም ዩናይትድ ስቴትስና የመንግሥታቱ ድርጅት መጠየቃቸው ይታወሳል።