ወጣቶች በመላው ኢትዮጰያ የሚሰማሩበት ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ አገልገሎት ምዝገባ ተጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስቴር ለሚቀጥሉት አስርት ዓመታት በተገባር ላይ የሚውል ብሄራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራም ለማስጀመር እድሜያቸው ከ 18 እስከ 35 ያሉ ስራ አጥተው የተቀመጡ ወጣቶችን እየመዘበ መሆኑን አስታውቆዋል፡፡ ይህ መርሃ ግብር ወጣቶች የሃገር ፍቅር ስሜት እንዲያዳበሩ፣ በራስ መተማመናቸው እንዲጨምር እና የተሻለ የስራ እድል እንዲኖራቸው የሚያገዝ መሆኑን በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጠሪ ተቋማት እና የስትራቴጂክ አጋርነት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ጀነራል ወይዘሮ አስማ ረዲ ተናገረዋል፡፡