ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ተማሪዎች እንደገና እንዲፈተኑ ተወሰነ

Your browser doesn’t support HTML5

በጦርነትና ግጭት ውስጥ ሆነው የተፈተኑና ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያላመጡ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከ2014 ዓ.ም መደበኛ ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ ተወሰነ። የትምህርት ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመሆን ዛሬ ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን በሰጠው መግለጫ፣ ከዚህ በፊት በተወሰነው የመቁረጫ ነጥብ ወደ ዩኒቨርሲቲ ከሚገቡት ተማሪዎች ውጭ ግጭት አለባቸው ከተባሉ ክልሎች ተጨማሪ ተማሪዎች እንደሚገቡ አስታውቋል፡፡ ጉዳዩን ሲከታተል የነበረው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እንዲሁም የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም የሚኒስቴሩን እርምጃ አድንቀዋል።