በሺሕ የሚቆጠሩ የባሕር ላይ ስደተኞች ሲተርፉ በሺሕ የሚቆጠሩት ደግሞ ሊቢያ እስር ቤት ገቡ

Your browser doesn’t support HTML5

ከሊቢያ ተነስተው በሜዲተራኒያን ባህር አቋረጠው ወደ ጣሊያን ለመግባት በጉዞ ላይ የነበሩና ባጋጠማቸው አደጋ የድረሱልኝ ጥሪ ያሰሙ 1500 ስደተኞች በጣሊያን የባህር ላይ ጠባቂዎች አማካኝነት ሕይወታቸው ተርፏል። በሌላ በኩል ደግሞ በሊቢያ የትሪፖሊን የባሕር ኃይል የሚቆጣጠረው ቡድን ከ1200 በላይ የሚሆኑ ወደ ጣሊያን ጉዞ የጀመሩ የባሕር ላይ ስደተኞችን ይዞ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ እስር ቤት አስገብቷቸዋል።