የመዝባ ገዳም መቃጠሉና መነኮሣት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ

  • ግርማይ ገብሩ

ኢሮብ-ትግራይ




Your browser doesn’t support HTML5

የመዝባ ገዳም መቃጠሉና መነኮሣት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ተሰማ


በአፋር ክልል የሚገኘው የመዝባ ገዳም ሆን ተብሎ የተለኮሰ የእሣት ቃጠሎ እንደደረሰበት የገዳሙ መነኮሣትና የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል።

በመነኮሳቱ ላይ ድብደባ መፈፀሙንም ምንጮች ጨምረው ገልጠዋል።

ድርጊቱ ያስቆጣው በመቶዎች የተቆጠረ ሰው ሰኞ፣ ግንቦት 19 / 2005 ዓ.ም ወደ መቀሌ ተጉዞ በተወካዮቹ አማካኝነት ለክልሉ መንግሥት አቤቱታ ማሰማቱም ተዘግቧል።

የአባላ ወረዳ አስተዳደር በበኩሉ ጉዳዩን ለማጣራት ወደ አካባቢው የፖሊስ ኃይል መላኩን አስታውቋል።

ለተጨማሪና ዝርዝር የተያያዘውን የግርማይ ገብሩን ዘገባ ያዳምጡ