ሕዝብንና ፓርቲን አንድ አስመስሎ የማቅረብ ትርክት እንዲታረም ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረውን ልዩነት ወደ ሕዝብ ለማዝለቅ የሚደረግ እንቅስቃሴ እንዲቆም ያሳሰቡ ሦስት የትግራይ ክልላዊ ፓርቲዎች፣ ሕዝብንና ፓርቲን አንድ አስመስሎ የማቅረብ ትርክትም እንዲታረም ጥሪ አቅርበዋል።

ሣልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ እና ውድብ ናፅነት ትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ የፌደራሉ መንግሥትም፣ የአንድን ፓርቲ ጉባኤ ጉዳይ፣ “ከክልሉ ሕዝብ አጠቃላይ ደኅንነት ጋራ ማያያዙ ተቀባይነት የለውም፤” ሲሉ ተቃውመዋል።

በፓርቲዎቹ መግለጫ ላይ፣ ከፌደራል መንግሥት እና ከህወሓት ቃል አቀባይ አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።