“የፌዴራሊስት ኃይል ፎረም" ተቋቋመ

Your browser doesn’t support HTML5

በመቀሌ ከተማ በተካሄደው "የፌዴራሊስት ኃይሎች" ጉባዔ የተገኙ ተሣታፊዎች "የፌዴራሊስት ኃይል ፎረም" ለማቋቋም መስማማታቸውን ባወጡት የአቋም መግለጫ አስታውቀዋል:: “ህገ መንግሥትና ኅብረ ብሔራዊ ፌዴራላዊ ሥርዓትን ማዳን!" በሚል መሪ ሃሳብ በተካሄደውና ትናንት ማምሻውን በተጠናቀቀው በዚህ መድረክ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምሁራንና የአገር ሽማግሌዎች መሣተፋቸው ተነግሯል።