የክልሎች ርእሳነ መስተዳድር እና የሁለቱ ከተሞች ከንቲባዎች በትግራይ ዳግም ግንባታ እንደሚሳተፉ አስታወቁ

Your browser doesn’t support HTML5

የሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች ርእሳነ መስተዳድር እና የሁለቱ የፌዴራል ከተሞች ከንቲባዎች፣ በዛሬው ዕለት በትግራይ ክልል ጉብኝት ሲያካሒዱ፣ ልኡካኑን የመሩት የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ፣ በክልሉ ዳግም ግንባታ ሒደት፣ ፓርቲያቸው እና መንግሥታቸው በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታውቀዋል፡፡

የዐማራ ክልል ርእሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፋለ እና የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ፣ የትግራይ ክልል አመራሮች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ባሕር ዳር ከተማንና ሠመራን እንዲጎበኙ ጋብዘዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ጌታቸው ረዳም፣ በየርእሳነ መስተዳድሮቹ የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸውን ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡