ሰላማዊ ሰልፍ - በመቀሌ

Your browser doesn’t support HTML5

በመቀሌ ከተማ ህገ መንግሥት ይከበር የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል። የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ የህዝብ ድምፅ አለ መስማት ከባድ ዋጋ ያስከፍላል ብለዋል። በሰልፉ ላይ ሕገ መንግሥት ይከበር፣ ብሄር ተኮር ጥቃት ይቁም እንዲሁም የውጭ ጣልቃ ገብነት ይቁም የሚሉ መፈክሮች ተደምጧል።