በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ በተነሳ ግጭት የሰው ህይወት አለፈ

Your browser doesn’t support HTML5

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ የሲቪሎችን ህይወት የነጠቀ ግጭት ዛሬ ማምሻውን መከሰቱ ተሰማ፡፡ ፖሊስ ለአደጋው መከሰት ምክንያቱ የግለሰቦች ግጭት መሆኑን አምኖ የጉዳቱን መጠን አጣርቼ እገልጻለሁ ብሏል፡፡ የአካባቢው ኗሪዎች ግን በግጭቱ ሰባት የፖሊስ አባላትና ሲቪሎች ሞተዋል እያሉ ነው፡፡