መድረክ አባሎቹ እየተገደሉና እየተዋከቡ መሆኑን ገልፆ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፃፈ

  • ሔኖክ ሰማእግዜር

በየነ ጴጥሮስ - ፕሮፌሰር /የመድረክ ሊቀመንበር/

መድረክ

Your browser doesn’t support HTML5

መድረክ አባሎቹ እየተገደሉና እየተዋከቡ መሆኑን ገልፆ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፃፈ

ግንቦት ውስጥ የተካሄደው የኢትዮጵያ ምርጫ በገዥው ፓርቲ አጠቃላይ አሸናፊነት ቢጠናቀቅም “ከምርጫው አስቀድሞና በማግሥቱ አባሎቼ ይገደላሉ፤ ይታሠራሉ፤ ይዋከባሉ” ሲል ተቃዋሚ ፓርቲው መድረክ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ ደብዳቤ ፃፈ።

እስካሁን አራት አባላቱ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በደቡብ ክልሎች መገደላቸውን የገለፀው የመድረክ መግለጫ የመንግሥት ባለስልጣናት በየአካባቢው የሚያካሂዷቸው ማስፈራራት፣ ድብደባ፣ እሥራትና ወከባን ሽሽት አሁንም አባላትና ደጋፊዎቹ ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ያትታል።

የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ሁኔታውንና ስለደብዳቤአቸውን ለቪኦኤ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡