የመድረክ መግለጫ
Your browser doesn’t support HTML5
"አሁን ሥልጣን ላይ ያለው የአስተዳደር ሥርዓት 'ፍጹም አምባገነናዊ ነበር' ካለው የቀደመው ሥርዓት በከፍተኛ አመራሩ ደረጃ “ለውጥ ቢያሳይም ለውጡ ግን ወደ ሕዝቡ አልወረደም" ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ተችቷል። "ሥርዓቱ አሁንም የመንግሥቱን ዋና ዋና ተቋማት ለወገናዊ የፓርቲ ዓላማ ማዋሉን ቀጥሎበታል" ሲልም ነቅፏል። በቅርቡ በፓርላማ የፀደቀውን የምርጫ ሕግም "አግላይ ነው" ሲል ከስሷል።