መድረክ በመቀሌ ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ

  • ግርማይ ገብሩ
የመድረክ የመቀሌ ስብሰባ የመድረክ መሪዎች

የመድረክ የመቀሌ ስብሰባ የመድረክ መሪዎች

የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ፓርቲ ባለፈው ዕሁድ መቀሌ ላይ ከፍተኛ ሕዝባዊ ስብስባ አካሂዷል።



መድረክ

መድረክ

Your browser doesn’t support HTML5

መድረክ በመቀሌ ሕዝባዊ ስብሰባ አካሄደ


የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ ፓርቲ ባለፈው ዕሁድ መቀሌ ላይ ከፍተኛ ሕዝባዊ ስብስባ አካሂዷል።

በስብሰባው ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ወጣቶች መሆናቸው ታውቋል። በስብሰባው የፓርቲው መሪዎች ስለፓርቲው ፕሮግራም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

“በኢትዮጵያ የብዙኃን ፓርቲ ሥርዓት አለ ሊባል አይችልም” ያሉት የመድረክ መሪዎች “መንግሥት በአስመራጭ ኮሚቴዎች ውስጥ የራሱን አባላት በማስገባት ምርጫውን ያኮላሻል” ብለዋል።

“በመንግሥት የቀበሌ መዋቅሮች የሃይማኖት ምርጫን በማስፈፀም ህገ መንግሥቱን የሚፃረሩ እርምጃዎችን ይወስዳል” በማለት ገዢውን ፓርቲ ከስሰዋል።

የአገር ልማትን በተመለከተም ከኢህአዴግ አስቀድሞ መድረክ አባይ መገደብ እንዳለበት ዕቅድ እንዳወጣ ጠቅሰው “የግድቡ ሥራ የገንዘብ መዋጮ ከመጠየቅ በስተቀር ተቃዋሚዎችን እና ሕዝብን ያገለለ መሆኑን እንቃወማለን” ብለዋል። “የግድቡ ሥራ ዕቅድ በፓርላማ ውይይት ተደርጎበት ያልፀደቀ ከመሆኑም በላይ በብክነት ለሚታወቀው ሳሊኒ መሰጠቱንም እንቃወማለን” ብለዋል።

ዝርዝሩን የመድረክ መሪዎችን ንግግርና የሕዝብ ተሣትፎ አጠናቅሮ ከያዘው ዘገባ ያዳምጡ።