“አዲሱ የመሬት ሊዝ አዋጅ ሕዝብን የኢሕአደግ ጭሰኛ ያደረገ ነው” ሲል መድረክ አወግዟል፡፡
ይህንንና መሰል የሕዝብን መብቶች የሚጋፉ አዋጆችን ለመቃወም በሚያካሂደው ትግል የሕዝብን ድጋፍ ጠይቋል፡፡
መንግሥት በበኩሉ አዋጁ ልማትን ለማፋጠን ይበጃል ይላል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በፅሁፍ ባወጣው መግለጫ “አዲሱ የሊዝ አዋጅ እጅግ ጨካኝ የሚባለው የደርግ መንግሥት ለሕዝቡ የሰጠውን የከተማ ቦታ ባለቤትነት እንኳ የነጠቀ የባሰ ጨካኝ ነው” በማለት ይኮንነዋል፡፡
በፅሁፍ መግለጫው እንደሚነበበው ደርግ ባወጣው አዋጅ ቁጥር 47/67 ላይ “አንድ ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ለመኖሪያ ቤት መሥሪያ የሚያውለው እስከ 500 ካሬ ሜትር የሚደርስ የከተማ ቦታ ሚኒስቴሩ ባወጣው መመሪያ መሠረት በይዞታ ሊሰጠው ይችላል፡፡ ባለ ይዞታ፣ የሟች ሚስት፣ ወይም ባል፤ ወይም ልጆቹ በቦታው ተተክተው የመጠቀም መብት ይኖራቸዋል” የሚለውን ይጠቅሣል፡፡
በመድረክ አስተያየት ይህንን እንኳ ደርግ የሰጠውን መብት የኢሕአዴግ መንግሥት ነጥቆታል፡፡
ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምኃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡