ወጣቱ ይሰራል ፣ ወጧቷ ትሰራለች የሚለው የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ፕሮግራም እኤአ በ2030 10 ሚሊዮን ወጣት ኢትዮጵያውያን ሥራ ለማስያዝ አልሞ በመስራት ላይ መሆኑን ይገልጻል፡፡ በ300 ሚሊዮን ዶላር የመነሻ በጀት በመመደብ የተነሳው ዓለም አቀፉ ግብረ ሰናይ ድርጅት፣ በተለያዩ የሙያ መስኮች የሰለጠኑ ወጣቶችን ክህሎት በማሳደግ ለሥራ ቅጥር ዝግጁ ያደርጋል፡፡
የራሳቸውንም ድርጅት ማቋቋም ለሚፈልጉም የፈጠራ ዝንባሌ ላላቸው ወጣቶችም የገንዘብ ድጋፍ ያመቻቻል፡፡ ከራሳቸውም አልፈው ሌሎቹን እንዲረዱ የሙያ የገንዘብና የአቅም ግንባታ ድጋፎችን እንደሚያደርግም ይናገራል፡፡ በአፍሪካ ወደ 30 ሚሊዮን በኢትዮጵያ ደግሞ 10 ሚሊዮን ወጣቶችን በአስር ዓመት ውስጥ ስራ ለማስያዝ ስለተነሳው ድርጅትና ፕሮጀክቶቹ የሚያስረዱን አቶ ዓለማየሁ ኮንዴ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በሩዋንዳ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ተወካይና የሥራ መሪ የሆኑትን አቶ ዓለማየሁ ኮንዴ ናቸው፡፡
አቶ ዓለማየሁ ኮንዴ በተለያዩ የዓለም አቀፍ የትምህርት፣ የረድኤትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ ላለፉት 25 ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በሩዋንዳ በርካታ የወጣቶችን የሥራ ፈጠራና ልማት ፕሮጀክቶችን መምራትን ጨምሮ፣ በደቡብምስራቅና አፍሪካ አገሮች ሰርተዋል፡፡ ቀደም ሲል በተለያየ ኃላፊነት ለፕላን ኢተርናሽናል የሰሩ ሲሆን አሁን ደግሞ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የሚያካሂደውን ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶች በምመራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ከኮቪድ 19 ጋር ተያይዞ ተጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ድርጅቶችና ለሥራ አጥነት የሚጋለጡ ዜጎችን በመታደግ ይሠራሉ፡፡ ድርጅታቸው ስለራሱ በሚሰጠው መግለጫ እንደሚገልጸው ፕሮጀክቶቹ በወጣቶች የሥራ ቅጥር ላይ ብቻ የተወሰነ አይደለም፡፡ እንደ ትምህርት ቤት ያሉ ማህበራዊ ተቋማትም ተተኪ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ፣ የኢንተርኔት ቴኮኖሎጂን የሚጠቀሙበትን መንገድ ያመቻቻል፡፡ ወጣቶች በተለይም ሴቶች፣ የተሻለ የሙያ ሥልጠና እንዲኖራቸው፣ የፋይንስ ድጋፍ ለሚያሻቸውም እንዲያገኙ በማመቻቸት ያግዛል፡፡ ለኮቪድ 19 ወረርሽኙ አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጡ ባለሙያዎችንም ይደግፋል፡፡ ኮቪድን በመካለካለም ሆነ ተጎጂዎችን መልሶ በማቋቋም የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተጠቃሚነት በማስፋፍትም ሆነ የፈጠራ ስራዎችን በማበረታት ይሠራል፡፡ በእነዚህና በሌሎች አገልግሎቶቹ ዙሪያ በኢትዮጵያ የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ተወካይ፣ አቶ ዓለማየሁ ኮንዴ ኮይራን አነጋግረናቸዋል፡፡
ቀሪውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5