የ26 ዓመቱ ፈይሳ ሌሊሳ በትናንትናው በሪዮ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን የብር ሜዳልያ ያሸነፈበትን ሩጫ አጠናቆ ሲገባ በኦሮሞ ተቃውሞ ጊዜ የተጀመረውና በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ምልክት የሆነውን እጅ ማጣመር ምልክት እያሳየ ገብቷል።
ዋሽንግተን —
ይህን በማድረጉም ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ የግድያ ፣ የእስራት እና ፓስፖርት መቀማት ስጋት ስላለበት ወደ ሀገሩ እንደማይመልስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ሜዳልያ ያመጣ ብሄራዊ ጀግና ነው፤ ሃሳቡን በነጻነት መግለጽ ይችላል፤ ወደ ሀገሩ ቢመለስ ምንም ዓይነት ጉዳት አይደርስበትም ብሏል።
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሌም ስለሚዋሽ በምን አምነዋለሁ? ብሏል።
በሌላ በኩል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፈይሳ ሌሊሳን የሕግ ድጋፍ እንዲያገኝ በሰዓታት ውስጥ ወደ 43 ሺሕ ዶላር ወይም ወደ 1 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር አሰባስበዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5