ማሊ ውስጥ ተፈፅሟል የተባለው ጭፍጨፋ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ተጠየቀ

Your browser doesn’t support HTML5

ማሊ ውስጥ በመንግሥቱ ወታደሮች እና በተጠርጣሪ የሩሲያ ቅጥር ወታደሮች እጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ተፈጽሟል በተባለ ግድያ ዙሪያ በነጻ አካል ምርመራ እንዲከፈት ተጠየቀ። ጥያቄውን ያቀረቡት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና የማሊ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ናቸው። ሙራ በምትባለው መንደር ግድያ መፈፀሙን የሚያትቱ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ የፀጥታ ኃይሎች 203 “ሽብርተኞች” ብለው የጠሯቸውን ሰዎች መግደላቸውን የማሊ ወታደራዊው መንግሥት አስታውቋል።

የዚህን ተቃራኒ አስተያየት የሰጡት እማኞች የማሊ መንግሥት ከሩስያውያን ቅጥር ተዋጊዎች ጋር እንደሚሠራ በግልጽ የሚያሳይ ማስረጃ ተገኝቷል።

/ከዋና ከተማዋ ከባማኮ የተጠናቀረውን የቪኦኤን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/