ማሕሙድ በ'ሬጌ' ሥልት!

ድምጻዊ ማሕሙድ አህሙድ እና ሙዚቀኛው ቶማስ “ቶሚ ቲ” ጎበና

"እኔ ጋሽ ማሕሙድን የማውቀውም የቀረብኩትም ያው በሙዚቃው ዘርፍ ነው። .. ከድሮ ጀምሮ .. ሁሌም ለአዲስ ነገር ቅርብ ሆኖ የማውቀው ጋሽ ማሕሙድ ነው። በዓለም ደረጃ የኢትዮጵያን ሙዚቃ በመወከል የሰራና አሁንም እየሰራ ያለ የሙዚቃ ሰው ነው።” ሙዚቀኛው ቶማስ ጎበና።

አንጋፋው ድምጻዊ ማሕሙድ አህሙድ ነው “አንችን .. አንችን” እያለ ከዚህ ቀደም ባልተጫወተበት የሬጌ ሥልት፣ ነገር ግን የብቻው ባደረገው አጨዋወት አዲሱን ዜማውን የሚያቀነቅልንልን።

“ቶሚ ቲ” .. የሙዚቃ ስሙ ነው .. ቶማስ ጎበና .. “አንችን” ከተሰኘው ከዚህ አዲስ የሙዚቃ ስልትና የቪዲዮ ሥራ ጀርባ ያለው የሥራው ጠንሳሽ እና አቀናባሪ።

የሙዚቃውን መውጣት መነሻ በማድረግ አጠር ያለ ቆይታ አድርገናል።

Your browser doesn’t support HTML5

“አንችን” .. ማሕሙድ በሬጌ ሥልት