በአማራ የአንበጣ መንጋ መቆጣጠር መቻሉ ተገለፀ

Your browser doesn’t support HTML5

በምሥራቅ አማራ አምስት ዞኖች ላይ ተከስቶ የነበረውን የአንበጣ መንጋ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን የኮምቦልቻ ዕፅዋት ጥበቃ ክሊኒክ አስታውቋል። አንበጣው የተፈራውን ያህል ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ሥር የዋለው በዘመናዊና በባህላዊ ዘዴዎች ታግዞ በተካሄድ ዘመቻ መሆኑ ተገልጿል። ይሁን እንጂ አንበጣው እንደገና ተቀፍቅፎ ሊወርርና ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ሥጋት አሁንም አለ።