የበረሃ አንበጣ መንጋን የመከላከል ሥራ

Your browser doesn’t support HTML5

በአፋር አካባቢ ተፈልፍሎ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ ለሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊዛመት ይችላል ተብሎ የተሰጋውን የበረሃ አንበጣ መንጋ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል። የበረሃ አንበጣውን ሙሉ በሙሉ ማጥፋትም ሆነ መከላከል ባይቻልም በሰብል ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ጥረት እንደሚደረግ ተገልጿል።