የአቶ ልደቱ አያሌው የፍ/ቤት ውሎ

Your browser doesn’t support HTML5

አቶ ልደቱ አያሌው በቀረበባቸው የህገወጥ ጦር መሳሪያ የመያዝ ክስ እንዲከላከሉ የምስራቅ ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለህዳር 16/ 2013 ዓ.ም ዛሬ ቀጠሮ ሰጥቷል። የሽግግር መንግሥት ሰነድ በማዘጋጀት የተከሰሱበት የኦሮምያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምስራቅ ምድብ አዳማ ችሎት በበኩሉ የአቶ ልደቱ አያሌውን የጤና ሁኔታ ተከትሎ በቀረበው የዋስትና ጥያቄ ላይ ብይን ለመስጠት ለህዳር 11/ 2013 ዓ.ም ቀጥሯል።