የሎሬት ለማ ጉያን ሥራዎች እንደሚያስቀጥሉ ልጆቻቸው ገለፁ

Your browser doesn’t support HTML5

ባለፈው ዓመት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት የሎሬት ለማ ጉያ ሥራዎችን ለማስቀጠል ፋውንዴሽን ማቋቋማቸን ቤተሰቦቻቸው ሰሞኑን ይፋ አድርገዋል።
በሕይወት እያሉ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው ሎሬት ለማ ጉያ በፍየል ቆዳ ላይ ስዕል በመሳል ብቸኛውና የመጀመሪያው ሰዓሊ ናቸው። የአባታቸውን ፈለግ መከተላቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ ሰላማዊ ለማ ፋውንዴሽኑ የተቋቋው የአባታቸውን ዓላማ ለማሳካት መሆኑን ተናግረዋል።