የኮንሶ ነዋሪዎች ከ50 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው የኮሚቴው አባል ነኝ ያሉ አቶ ገመቹ ጎንፋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ጥያቄውን ለመመለስ እና ችግሩን ለመፍታት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ከሕዝብ የተመረጡ 23 የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ገምቹ ገንፌ የኮንሶ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት ችግር ላይ መሆኑን ይናገራሉ።
ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል፣ ለደሃ ደሃ የሚሰጥ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተቋርጧል እንዲሁም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸውን ይናገራሉ።
ሌሎች ነዋሪዎችም ይህ ተቃውሞ ለደሃ ደሃ የሚደረገው የምግብ ዋስትና ድጋፍ እንዲቋርጥ ምክንያት እንደሆነናቸው ይገልፃሉ።
የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ አልተከፈላቸውም፣ ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል፣ ሰዎች በነፃነት መንቀሳቀስ አልቻሉም ሲሉ ይናገራሉ። የወረዳው አስተዳዳሪ በበኩላቸው ይህን ጥያቄ የሚያነሱት በባህል የተደራጁ ቡድኖች ናቸው ይላሉ።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5