“ተሰደን ጫካ ከገባን አምስት ወር አስቆጥረናል” ያሉ በኮንሶ በሕዝብ እንደተመረጡ የሚናገሩ የኮሚቴ አባላት ናቸው

ኮንሶ /ፎቶ ፋይል/

በኮንሶ የሕዝብ ጥያቄን ለማስመለስ በመነሳታቸው ተሰደው ጫካ ከገቡ አምስት ወር እንዳለፋቸው በሕዝብ እንደተመረጡ የሚናገሩ የኮሚቴ አባላት ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።

በኮንሶ ሰዎች አሁንም በጅምላ እንደሚታሰሩ፣የኮንሶን ሕዝብ ወክለው ጥያቄ ያቀርቡ የነበሩ የኮሚቴ አባላት የተወሰኑት መታሰራቸውን አብዛኞቹ ደግሞ መኖሪያ መንደራቸውን ትተው መሰደዳቸውን “እኛም በስደት ጫካገብተን ነው የምናነጋግራችሁ”ያሉ በሕዝብ እንደተመረጡ የሚናገሩ ሁለት የኮሚቴ አባላት ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ።

የክልሉን መንግስት ቃል አቀባይ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም እንዳገኝን ምላሻቸውን ይዘን ሌሎች የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግረን ለመመለስ ጥረት እናደርጋለን።

ጫካ ውስጥ መኖር ከጀመሩ አምስት ወር እንደሆናቸው ገልጸው መፍትሄ አተናል ያሉትን አቶ ገመቹ ገንፌ እና አቶ ለሜታ ቀቤ ያነጋገረቻቸው ጽዮን ግርማ ነች።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Your browser doesn’t support HTML5

“ተሰደን ጫካ ከገባን አምስት ወር አስቆጥረናል” ያሉ በኮንሶ በሕዝብ እንደተመረጡ የሚናገሩ የኮሚቴ አባላት ናቸው