በኮንሶ ዞን እና በአሌ ልዩ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት አስር ሰዎች ተገደሉ
Your browser doesn’t support HTML5
በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን እና በአሌ ልዩ ወረዳ ነዋሪዎች መካከል ዳግም በተቀሰቀሰ ግጭት ከሁለቱም ወገን አስር ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች በስልክ ገለፁ። አንድ የመንግሥት ባለሥልጣን እና ሁለት የደቡብክልል የልዩ ኃይል አባላት እንዲሁም ሦስት ሲቪሎች መገደላቸውን የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ገልጿል።
በቀደመው የሁለቱ አካባቢዎች ግጭት ግን አራት ሲቪሎች መገደላቸውን አስታውቋል።