Your browser doesn’t support HTML5
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን ተቀብለው ሲያነጋገሩ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከኛ ጋር በጣም ብዙ ሰርተዋል ብለዋል።
“ በኢትዮጵያ ስላለው የጤና ጥበቃ ጉዳይ ብዙ ተነጋግረናል። በደቡብ ሱዳን ያለውን ሂደት ስለማንቀሳቀስ ጉዳይም ተወያይተናል። ኢትዮጵያ በተለይም ሀገሮችን በማቀራረብ ተግባር፣ ተኩስ እንዲቆም በማድረግና ተቀናቃኝ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲያመሩ በማግባባት ረገድ የመሪነት ቦታ ይዛ ቆይታለች። ሶማልያ ውስጥ በተካሄደው የሽግግር ጉዳይም ኢትዮጵያ ለኛ ቁልፍ ሚና ነው ያላት። ለዚህ ተግባርዋም እጅግ እናመሰግናለን። በእውነቱ የክልሉ መሪ ናት።” ሲሉ አሞግሰዋል።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በበኩላቸው የኢትዮጵያና የ United States ግንኙነት እየሰረጸ ሄዷል ብለዋል።
" በአከባቢው ሰላም፣ መራጋጋትና ጸጥታ እንዲሰፍን ማድረግ የወቅቱ የትብብራችን ምሰሶ ነው። ከዛ ሌላ ደግሞ United States እና ኢትዮጵያ የአሜሪካ መዋዕለ-ነዋይ ፍሰት ኢትዮጵያ እንዲገባ አበክረን እየሰራን ነው። በዚህ መድረክና ጉባኤ ላይም ትልቅ እድል አግኘተናል። በሀገሪ መዋዕለ-ነዋይ የማፍሰስ ፍላጎት ካላቸው በርካታ የ United States ኩባንያዎች ጋር ስንሰራ ቆይተናል።" ማለታቸው ተጠቅሷል።