ኬኒያ በቤት ሠራተኝነት ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለሚሄዱ ዜጎቿ ሥልጠና መስጠት ጀመረች

Your browser doesn’t support HTML5

የኬኒያ ባለሥልጣናት በቤት ሠራተኝነት ተቀጥረው ወደመካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች ለሚሄዱ ዜጎች መብታቸውን እንዲያውቁ ሥልጠና በመስጠት ላይ ናቸው፡፡ ይህ ሥልጠና መሰጠት የተጀመረው ሠራተኞቹ ድብደባ፣ መደፈር እና ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙባቸው ለበርካታ ዓመታት የወጡትን ሪፖርቶች ተከትሎ ነው፡፡ ካለፈው ኅዳር ወር ወዲህ የተጠቀሱት አድራጎቶች የተፈጸሙባቸው ቢያንስ ሃያ ሦስት ኬንያውያን አንዳሉ ሪፖርት የደረሳቸው መሆኑን የኬኒያ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡ የሚበዛው ሳውዲ አረብያ ውስጥ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡

ከናይሮቢ ቪክቶሪያ አሙንጋ ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ወደ አማርኛ መልሰዋለች።