የኬንያ ት/ቤቶች ሊከፈቱ ነው
Your browser doesn’t support HTML5
በታህሳስ 26 በመላው ኬንያ ያሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ። ኬንያ በሚመጣዉ ታህሳስ 26 በሀገሩ ያሉ ሁሉም ተማሪ ቤቶች እንዲከፈቱ ዝግጅት ማድረጓን አስታወቀች። የሀገሪቱ ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔዉ የሀገሩ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በኬንያ አሁንም በአሳሳቢ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን መንግሥት አስታውቋል።