በናይሮቢ የተገረዙ ሴቶች ግርዛቱን የሚቀለብስ ቀዶ ጥገና ተደረገላቸው

Your browser doesn’t support HTML5

እዚህ ናይሮቢ ውስጥ ለተኘገችው ይህቺ ሴት ይህ ቀን ትልቅ ነው፡፡ እርሷና ሌሎች ሃምሳ ሦስት በልጅነታቸው የተገረዙ ሴቶች ዛሬ ግርዛቱን የሚቀለብስ ቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡ “ካሊቶርኤድ”በሚል መጠሪያ ከተዋቀረው የዩናይትድ ስቴትስ ድርጅት የመጡ ዶክተሮች የሴቶቹን የተቆረጠ ብልትና በመቆረጡም ያጡትን ስሜት በቀዶ ጥገና ሊመልሱ ይሞክራሉ፡፡