ኬኒያ በመጪው ምርጫ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ምክትል ፕሬዚዳንት ልትመርጥ ትችላለች

  • ቆንጂት ታዬ

Your browser doesn’t support HTML5

ኬኒያ የፊታችን ማክሰኞ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ከሚፎካከሩት ከአራቱ እጩዎች መካከል ውድድሩን እየመሩ ያሉትን ራይላ ኦዲንጋን ጨምሮ ከሦስቱ ጋር ለምክትል ፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩት ሴቶች ናቸው። ይህም “በሀገሪቱ ፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት ይችላል” በሚል በተንታኞች ተገምቷል።

የሀገሪቱ ሴት የፖለቲካ ሰዎች እንዲህ ያለ ታሪካዊ ደረጃ ላይ ለመድረስ የተጓዙበት ጎዳና ቀላል እንዳልሆነም ይናገራሉ።