የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ በመሬት መብቶችና በምግብ ዋስትና ላይ ማብራሪያዎችን አዳምጧል፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ በመሬት መብቶችና በምግብ ዋስትና ላይ ማብራሪያዎችን አዳምጧል፡፡
በማብራሪያው ወቅት “ታላቁ የመሬት ቅርምት” እየተካሄደ ነው እየተባለ በሚወራበት የአፍሪካ ክፍል ላይ ጥያቄዎችና ትችቶች ተሰምተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት በኪራይ እየሰጠ ያለው መሬት የውጭ ሃገር ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የሕንዱ ግዙፍ አግሮ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ካሩቱሪ ግሎባል ብዙ ጊዜ ይጠቀሣል፡፡
ካሩቱሪ ከሁለት መቶ ሺህ ሄክታር በላይ የሚሆን ለም የሚባል መሬት በጋምቤላ ክልል ውስጥ አከራይቶታል፡፡
በኦሮሚያም በባኮ ከተማ አቅራቢያ ካሩቱሪ እንዲሁ ሰፊ የእርሻ ማሣ የተሰጠው መሆኑ ይታወቃል፡፡
እነዚህን ስምምነቶች በተመለከተ በርካታ የአካባቢ ጥበቃና የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች የሆኙ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች ተቃውሞ ሲያሰሙ ይስተዋላሉ፡፡
የካሩቱሪ ግሎባል መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ የሆኑት ራም ክሪሽና ካሩቱሪ ከቪኦኤ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል፡፡
ዘገባውን ያዳምጡ፡፡