የቃሊቲ አዛዥ ተይዘው እንዲቀርቡ ታዘዘ

Your browser doesn’t support HTML5

በነ አቶ ጀዋር መሐመድ ህክምና ላይ ፍርድ ቤት ያሳለፈው ውሣኔ ያልተፈፀመበትን ምክንያት አዛዥ ቀርበው እንዲያስረዱ ታዝዘው የነበሩት የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ዛሬም ባለመቅረባቸው ከነገ በስተያ ሐሙስ፤ የካቲት 18/2013 ዓ.ም. ታስረው እንዲቀርቡ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዝዟል።
በሌላ በኩል የጠቅላይ አቃቤ ህግን ይግባኝ የተመለከተው ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የላንድማርክ ሆስፒታል የሀኪሞች ቡድን እነ አቶ ጀዋር መሐመድ ያሉበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሄዶ የህክም አገልግሎት እንዲሰጥ ወስኗል።